=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ሙስሊሞች በኡኹድ ጦርነት ተሸንፈው በእጃቸው የነበረውን ድል ተነጥቀው ፣ ሽንፈትን ተከናንበው አዝነውና ተክዘው በተመለሱ ጊዜ አሏህ ሙዕሚኖች ድል የሚያደርጉበትን መንገድ እንዲህ ሲልነበር ያመላከታቸው።
አሏሁ አዘወጀል በቅዱስ ቃሉ በሱረቱል ኢምራን አንቀፅ 139 ላይ እንዲህ ይላል፦
=<({አል-ቁርአን 3:139})>=
{139} ደካሞች አትሁኑ፤ አትዘኑም። በእርግጥ እውነተኛ አማኞች ከሆናችሁ የበላዮች(አሸናፊዎች) ትሆናላችሁ።....Read More
እናት ሐግራችን ኢትዮጲያ ብዙ አንባገነኖችን ከጥንት ጀምሮ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ እያስተናገደች ትገኛለች። በጥንት ጊዜ የነበሩ አምባገነኖች በቀጥታም ሆነ በተዘዋሪ እራሳቸውን ልክ እንደ ፈጣሪ ወይም ደግሞ ከፈጣሪ ዘንድ እንደተሾሙ አድርገው ሲያቀርቡልን ኑረዋል። ይህን ያደርጉበት የነበርው ዋነኛው ምክኒያት በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖራቸውና ህዝቡ ሳይወድ በግድ በነሱ አስተዳደር ውስጥ እንዲሆን ነበር። አሁን ያሉ አምባገነኖችም ቅርፃቸውን ቀይረው የህገመንግስት የበላይነት የሚል መፈክር አንግበው እንደፈለጉ በሚተረጉሙትና በሚሽሩት ህገመንግስት ህዝቡን ከጫማቸው ስር ማድረግ ይሻሉ። ታዲያ ዱሮ የነበሩትንም ሆነ አሁን ያሉትን አንባግነኖች አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር በኢስላም ላይ የዘመቱ የጥፋት ሃይሎች መሆናቸው ነው።
በአፄዎቹ ዘመን የነበሩ አንባገነኖች በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የረጅም ጊዜ እምነትንም ሆነ ህዝብን የማጥፋት ጦርንት አውጀው ነበር።....Read more
እኛ ሙስሊሞች በዲነል ኢስላም አስተምህሮት ስንኖር መዋደድ ፣ መተነነስ ፣ ሰላም ፣ መቻቻል ፣ ወንድማማችነት እና አንድነት የሚሉ እሴቶችን ተላብሰን መሆን አለበት። ምክኒያቱም እነዚህ ነገሮች የነዛ ብርቅየ ሶሃቦች ማንነት ፣ የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) አስተምህሮት ውጤቶች ሲሆኑ ልዑል ሃያል የሆነው አምላካችን አሏህ ወደ አንድነት እና ወደ ወንድማማችነት ጎዳና እንድንመጣና በነዚህ እሴቶች እንድንኖር ያስገድደናልና ነው።
አሏሁ አዘወጀል በቅዱስ ቃሉ በሱረቱል ኢምራን አንቀፅ 103 ላይ እንዲህ ይለናል፦
=<({አል-ቁርአን 3:103})>=
{103} ሁላችሁም በአሏህ ገመድ ተሳሰሩ፤ አትከፋፈሉም። እርስ በርስ ጠላቶች በነበራችሁ ጊዜ አሏህ በእናንተ ላይ የዋለውን ውለታ አስታውሱ ልቦቻችሁን አስተሳሰረ። እናም በችሮታው ወንድማማቾች ሆናችሁ። በእሳት ጉድጎድ አፋፍ ላይ በነበራችሁም ጊዜ ከሷም ጠበቃችሁ። እናም ትመሩ ዘንድ አሏህ አንቀፆቹን ግልፅ አደረገላችሁ።
ከላይ በተጠቀሰው የቁርአን አንቀፅ አሏህ(ሱ.ወ.ተ) በአሏህ ገመድ ማለትም በቁርአን እና በረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ሱና ተሳሰሩ ካለ ብኋላ መከፋፈልን ወይም ቡድንተኝነትን እና ቲፎዞ ፈላጊነትን ሐራም ማድረጉን እንረዳለን።
ይሁንእንጅ አንዳንድ እራሳቸውን እንደ ሙወሂድ ሌሎችን ልክ እንደ ሙሽሪክ እና እንደ ቢድእይ የሚመለከቱ ሰዎች ወደ አንድነት የሚጣሩትን ሰዎች ጥሪያቸው ከተውሂድ ውጭ እንደሆነ በማስመሰል ይህ ኡማ አንድ ሊሆን የሚችለው በተውሂድ ብቻ ነው ሲሉ።....Read more
ሰዎች ሆይ! ከዚህ አመት ቡኋላ በድጋሚ ከናንተ መካከል መሆኔን አላውቅምና ጆሮዋችሁን አውሱኝ። ስለዚህ የምነግራችሁን ነገር በደምብ አድምጡ፤ ንግግሬንም ዛሬ እዚህ ቦታ ላይ ለሌሉ ሰዎች አድርሱ።
ሰዎች ሆይ! እንደምታውቁት ይህ ወር ፣ ይህ ቀን እና ይች ከተማ የተቀደሱ ናቸው። እናም የእያንዳንዱ ሙስሊም ህይወት እና ሃብት ንብረት የተቀደሰ አደራ እንደሆነ እወቁ። በአደራ መልክ የተሰጣችሁን ሸቀጦች(ንብረቶች) ለባለቤቶቻቸው መልሱ። ማንንም አትጉዱ፤ ማንም አይጎዳችሁምና። በእርግጥም ጌታችሁን እንደምትገናኙ እና ስራዎቻችሁን እንደምትተሰሳቡ እወቁ። አሏህ አራጣ መብላትንም ከልክሏችኋል፤....Read More
ይህ መጽሐፍ የተረጎምኩት ከኢማም ሙሐመድ ኢብን አብዱልወሃብ "ማዕነቱ ጣኡት" ከሚለው ፅሁፋቸውና ከዶ/ር ሙሐመድ ቢን አብዱ-ረህማን አልኩመይስ ማብራሪያ ሲሆን በውስጧም አራት ምዕራፎች አሏት።
ከዚህ በተጨማሪ በየምዕራፍ መጨረሻ ማጠቃለያና እራሳችነን የምንፈትንባቸው መልመጃዎች ተካተዋል።
የላኢላሃ ኢለሏህ የምስክርነት ቃል የጀነት ቁልፍ ነው። ታዲያ ይህ የምስክርነት ቃል መሉ ይሆን ዘንድ ቅድመ ሁኔታዎች አሉት። የቁርአን አናቅፅቶችን እና የረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች ብናጠና የሸሃዳ ቅድመ ሁኔታዎች በቁጥር ስምንት ወይም ዘጠኝ እንደሆኑ እንረዳለን። ሆኖም ሁላችነም እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች በህይወታችን የራሳችነን የእምነት ምስክርነት ያሟላን መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብናል። ነገሮች ከመበላሸታቸውና አቅጣጫ ስተው ከመሄዳቸው በፊት እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች ለሟሟላት የቻልነውን ሁሉ ማድረግ አለብን።
ይህ መጽሐፍ ስለ ኢስላም ግንዛቤ ለሌላቸው ሰዎች እጥር ምጥን ባለ መልኩ እውቀት የሚያገኙበት እውቀት ያላቸውም ለመሸምደድ የሚያመች በመሆኑ እውቀታቸውን የበለጠ የሚያዳብሩበት ወይም ለማስተማር የሚረዳ ሆኖ ስላገኘሁት ወደ አማርኛ ተርጉሜዋለሁ። ጠቃሚ ሆኖ እንደምታገኙት ተስፋ አደርጋለሁ።
በዚህ መፅሐፍ ከተዳሰሱ አርዕስቶች መካከል የኢስላም ምንነት ፍች ፣ አምስቱ የኢስላም ህጎች ፣ ጦሃራ ፣ የቆሻሻ አይነቶችና የማስወገጃ መንገዶቻቸው ፣ ኢስቲንጃ ፣ ውዱዕ ፣ ጉሱል ፣ ተየሙም ፣ ሶላት ፣ አርካኑ ሶላት ፣ የኢድ ሶላቶች ፣ ዘካና ሃጅ ወ.ዘ.ተ አርዕስቶች ተዳሰውበታል። በየምዕራፉ የተነሳውን አርዕስት ምንያህል እንደተረዳነው እራሳችነን ለመፈተሽ ከእያንዳንዱ ምዕራፍ መጨረሻ ላይ ጥያቄዎች ተካተውበታል። አንብበን የምንጠቀምበትና ሌሎች እህት ወንድሞቻችነን የምንጠቅምበት ያድርግልን።
ዘመኑ የውድድርና የሽቅድድም ዘመን በመሆኑ የሰው ልጅ ሩጫው ለዱንያና ዱንያ ለያዘችው ነገር ሆኗል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት ሰዎች ስራ ማጣት ፣ በቂ ገቢ አለማግኘት ፣ እራሳቸውን የሚያስተዳድሩበት ነገር አለማግኘት ፣ ትዳር መስርተው የሚኖሩበት ወይም ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩበት በቂ ሲሳይ ማጣት ያስጨንቃቸዋል። ሆኖም ይህን ችግር ለማስወገድ በአሏህ መንገድ ላይ ሆነው ከመፈለግ ይልቅ ሃራም የሆኑ የለውጥ ጎዳናዎችን ሲጠቀሙ ይስተዋላል።
በዚች አነስተኛ መጽሐፍ ውስጥ እንዴት ቀናውን የአሏህ መንገድ ተከትለን ሲሳይ ማግኘት እንደምንችል ከቁርአንና ከሐዲስ ማስረጃዎችን በማጣቀስ የተወሰኑ ጠቋሚ ነጥቦች ተዳሰዋል። መልካም ንባብ!
ሁሉም ሰው ህይወቱ መልካም ፍፃሜ ያገኝለት ዘንድ ይመኛል ያልማል። አብዛሃኛው ወጣቱ ክፍልም ነገን በተስፋ እየጠበቀ ወጣትነቱን ተደስቶበት በማሳለፍ ሃምሳዎቹና ስልሳዎቹ የእድሜ ክልል ላይ ወደ አሏህ እንደሚመለስብ ያስባል። ትልቁ ጥያቄ ግን ነገን ስለመኖርህ ዋስትናህ ምንድነው? ነገ የተቃና ሰው እንደምትሆን ምንድነው ማረጋገጫህ? የሚል ነው።
በዚች አነስተኛ መጽሐፍ የመልካም ፍፃሜ ምንነት ፣ ምልክቶቹ ፣ የመጥፎ ፍፃሜ ምንነትና ምልክቶቹ እንዲሁም ወጣቶች ላይ የሚስተዋሉ የተሳሳቱ ግንዛቤዎችና ቁርአናዊ ግሳፄዎች ተዳሰውበታል ያንብቡት!
ወጣቶች ደስታን ለማጣጣም ወይም ከጎደኞቻቸው ጋር ላለመለያየት ወይም ደግሞ ዱንያዊ ኑሯቸውን ለማቃናት ሲሉ ከአሏህ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት ያቋርጣሉ። አሉ የተባሉ ሃራም ነገሮችንም ይሰራሉ። የሚፈልጉትን ነገር በሃላል መንገድ ማግኘት ሲችሉ አሏህን በማመፅ ላይ ይፈልጋሉ።
ወቅቱ ወጣቱ ክፍል ለወጣትነት ጊዜው ትኩረት የማይሰጥበት ፣ ለዲኑ ግዴለሽ የሆነበት ፣ ከእውቀት ይልቅ አሉቧልታን ያስቀደመበት ፣ ከመስጊድ የራቀበት ፣ አዋዋሉ የማያምርበት ፣ ለጊዜ ዋጋ የማይሰጥበት የድንቁርና ጊዜ በመሆኑ ይችን ፅሁፍ ልፅፍ ወደድኩ አውርደው ያንብቧት!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
|
---|